• Admin

“መንገድህን ለእግዚአብሔር አደራ ስጥ…”

በአለፉት ሶስት ወራት ጌታ በኢትዮጵያ አድቬንቲስት ቤተክርስትያን ከመስከረም 2010 ጀምሮ እስከ ህዳር መጨረሻ ድረስ ያደረገዉን ድንቅ ስራ ሳበሰር ታላቅ ደስታ ይሰማኛል፡፡ በኢትዮጵያ ዉስጥ ወንጌል የአልገባባቸዉ እጅግ ብዙ ስፈራዎች አሉ፡፡ ከእነዚህም መሀል አንዱ የዳሰነች ጎሳ ሲሆን፣ ጌታ ፈቅዶ በመጋቢት ወር አዲስ ከተቓቓመዉ ፊልድ ጋር በመተባበር፤ እኛና የምስራቅ ኬንያ ዩንየን ኮንፈራንስ ጋር ሆነን ይህንን ጎሳ ለመድረስ የነበረን እቅድ በተግባር ላይ ለማዋል ቦታዉን እንዲያጠኑ ሁለት ፓስተሮችን ላክን እነሱም፤ 1. ፓስተር ነጋሽ ጴጥሮስ የፊልዱ ፕሬዝዳንት 2. ፓስተር አባይ አያናዉ የግሎባል ሚሽን ዳሬክተር፡፡


እነሱም ቦታዉ ምን እንደሚመስልና ያለዉን ሁኔታ አጥንተዉ በመምጣት በሰኔ ወር ላይ መረጃ ሰጡን እኛም ወደያዉኑ ወንጌላዊ እንዲልኩና እኛም ደግሞ ደመወዙን እንደምንችል አሳወቅናቸዉ ፡፡ እነሱም ሀሳቡን ወዲያዉኑ ተግባራዊ በማድረግ ወንግላዊ ላኩ፡ ጌታም ያንን ወንግላዊ በመጠቀም ብዙ ነፍሳትን ሰጠን ፡፡ ስለዚህ ከመስረም 11 ጀምረን እስከ መስከረም 30 ድረስ የወንጌል ጥረት ለማድረግ ጉዞ ወደ ዳሰነች ወረዳ ቀጠልን፡፡ ዳሰነች ወረዳ የሚገኘዉ በጂንካ ዞን ዉስጥ ነዉ ፡፡ ከአዲስ አበባ 977 ኪሎ ሜትር ሲሆን ከአርባምንጭ 500 ኪሎ ሜትር ከጂነካ ደግሞ 200 ኪሎሜትር ነዉ፡፡ ከዩንየን እኔና ሲስተር ገላኔ ኩመራ የጤና ክፍል ሃላፊ፤ እኔ ደግሞ የኢቫንጀሊዝም ዲፓርትሜንት ወክለን ጉዞ ወደ ወላይታ ሶዶ ቀጠልን ከዚያም ዮናታን ዮሃንስ የሚባል የጤና ባለሙያ ከዚህ በፊት እዚያ ወረዳ የሰራና የአዋሳ ታቦር ቤተክርስትን ፈቃደኛ ወንጌላዊ የሆነ፤ እንዲሁም በአዋሳ ከተማ ጤና ቢሮ የሚሰራ በጣም ጠንካራ የሆነ ወጣት ነዉ፡፡ በተጭማሪም የደቡብ መሃከለኛ ሰበካ ዋና ፀሐፊ ፓስተር ዳዊት ጉድኖ እንዲሁም እዚያ በምንቆይበት ወቅት ምግብ የምታበስልልን እህት ምትኬ ሆነን መስከረም 9 ቀን ከወላይታ ተነሳን ቀኑን ሁሉ ስንጋጓዝ ዉለን ከለሊቱ 7 ሰአት ገደማ ደሰነች ወረዳ ኦሞራቴ ከተማ ደረስን፡፡ ጉዞ ሁለት ቀን ፈጀብን፡፡


ከዚያም ከሳምንት በኃላ ከኬንያ የሚመጣዉ ቡድን ከብዙ መከራ በኃላ በእግዚአብሔር እርዳታ ከእኛ ጋር ተቀላቀሉ፡፡ ቁጥራቸዉ 27 የሚሆኑ ሰዎች በእምነት የማያዉቁትን ቦታ ለመድረስ 5 ቀን ከተገዋጓ ዙ በኃላ ከአኛ ጋር ተቀላቀሉ፡፡ አምስት ቀን የቆዩበት ዋናዎቹ ምክንያቶች ሁለት የጭነት መኪናዎች፤ 1 አዉቶቢስና አንድ ላንድ ክሮዜል መኪና ይዘዉ ሲጓዙ አንዱ መኪናቸዉ ተበላሽቶባቸዉ ነበር ፡፡ በመጨረሻም የኬንያን ድንበር አልፈዉ ኢትዮጵያ ከገቡ በኃላ ዝናብ ስለነበረ መኪናዎቻቸዉ በአሻዋ ስለተዋጡባቸዉ ነበር፡፡


ከ5 ቀናት በኃላ እኛም በአሻዋ ወደተያዙበት ስፍር ተጉዘን ከእነሱ ጋር በመቀላቀል ይዘናቸዉ ወደ ኦሞራቴ ከተማ ተመለስን፡፡ እዚያ ደግሞ ሌላ ከባድ ችግር ገጠመን መኪናዎቻችን በጉምሩክና በኢሚግሬሽን ታሰሩ፡፡ ከብዙ ልፋትና ዉጣዉረድ በኃላ መድሃኒቶቻችንና ልብሶችን አስረክበን ሌሎች ንብረቶቻችን አስለቀቅን፡፡ ዋናዉ ቁም ነገር የ4ቱ ቤተክርስትያን መስርያ የሚሆኑ እቃዎቻችንና ምግቦቻችን መለቃቸዉ ነዉ፡፡ ይህንን ቡድን ይመሩ የነበሩት 1. ዶ/ር ኦኪነዶ ክንያዊ ሲሆኑ 2. ዶ/ር ፍስሀ ጸጋዬ፤ የፓ/ር ጸጋዬ ተገኔ ልጅ ናችዉ፡፡ የእዚህ ፕሮግራም ጠንሳሽ እነዚህ ሁለት በምስራቅ መሀከለኛዉ አፍሪካ ዲቪዥን በድፓርትሜንት የሚያገለግሉ ወንድሞች ናቸዉ፡፡


የዳሰነች ጎሳ 75% በኢትዮጵያ 25% ደግሞ በኬንያ የሚገኝ ጎሳ ሲሆን አርብቶ አደሮች ናቸዉ፡፡ ቋንቋቸዉም አንድ ነዉ በኢትዮጵያ ያሉት አማርኛ ይሞክራሉ በኬንያ ሉት ደግሞ ስዋሂሊ ይናገራሉ፡፡ ከኦሞራቴ ከተማ የኬንያ ድንበር 28 ኪሎ ሜትር ይርቃል ፡፡ ከዚያም ለ10 ቀናት በአራት ቦታዎች የወንጌል ጥረት አድርገን ጌታ 406 ሰዎች በጥምቀት ወደ ቤተክርስትያናችን እንዲቀላቀሉ እረዳን፡፡ እንዲሁም ለ4ቱም ቦታዎች አንድ ቤተክርስትያን ሰረተናል፡፡ አገሩ በጣም ሞቃት ስለሆነ በብረት ማእዘን የተሰሩ ሲሆኑ ጣራ ብቻ እንጂ ግድግዳ የላቸዉም፡፡ በዚህ በአጭር ጊዜ ዉስጥ ይህንን ሁሉ እንድንሰራ ጉልበትና ኃይል የሰጠንን አምላክ የተመሰገነ ይሁን፡፡ እነዚህ በጥምቀት ቤ/ ክትንን የተቀላቀሉ ወንድሞችና እህቶች በእምነታቸዉ ፀንተዉ እንዲቆሙ በጸሎታችሁ አስቡዋቸዉ፡፡ ጌታ ይባረካችሁ


ፓስተር አለሙ ኃይሌ

43 views0 comments

Recent Posts

See All

እንደምን አደጋችሁ?

በፓስተር መላክ አለማየሁ ካለፈው የቀጠለ ባለፉት ሁለት ክፍሎች በመንፈሳዊ ሕይወታችን ስለ ማደግ ጠቅለል ባለ መልኩ መግቢያ የሚሆንን ሃሳብ ለማየት ሞክረናል። የፈጠረንና የዋጀን እግዚአብሔር ለእኛ ያለው አላማ እለት እለት ወደ በረከቱ ሙላት እንድናድግ መሆኑ ቃሉ አስተምሮናል። እንዲሁም፣ በጸጋ ማደግ የሚከቱትን ሦስት

እንደምን አደጋችሁ?

ካለፈው የቀጠለ “እኔ ተከልሁ፤ አጵሎስ ውሃ አጠጣ፤ ያሳደገው ግን እግዚአብሔር ነው። ስለዚህ የሚያሳድግ እግዚአብሔር እንጂ፣ የሚተክልም ሆነ ውሃ የሚያጠጣ ምንም አይደለም። የሚተክልም ሆነ የሚያጠጣ አንድ ናቸው፤ እያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን የራሱን ሽልማት ይቀበላል። እኛ ከእግዚአብሔር ጋር አብረን የምንሠራ ነንና

"ለዘንድሮ ብቻ ተዋት"

በአገራችን 2010 አመተ ምህረት ከገባ 3 ወር አለፈው። በምዕራብ አገሮች ደግሞ በቅርቡ 2018 ይገባል። ሁሉም በየበኩሉ አዲሱን አመት ለመቀበል ሽርጉድ ይላል። በአገራችን "እንኳን ከዘመን ወደ ዘመን አሸጋገራችሁ" እንባባላለን። በምእራብ አገሮች ደግሞ "happy new year" ይባባላሉ። ትኩር ብለን ካሰብንበት ያ

የኢትዮጵያ አድቬንቲስት ቤተ ክርስቲያን ዋሺንግተን ዲሲ

© 2018 Ethiopian Seventh-day Adventist Church Washington DC

1700 Powder Mill Rd, Hillandale, MD 20903, U.S.A  301-356-5259

  • Facebook Social Icon
  • YouTube Social  Icon
  • Google Places Social Icon
  • Twitter Social Icon