• Admin

እንደምን አደጋችሁ?

ካለፈው የቀጠለ

“እኔ ተከልሁ፤ አጵሎስ ውሃ አጠጣ፤ ያሳደገው ግን እግዚአብሔር ነው። ስለዚህ የሚያሳድግ እግዚአብሔር እንጂ፣ የሚተክልም ሆነ ውሃ የሚያጠጣ ምንም አይደለም። የሚተክልም ሆነ የሚያጠጣ አንድ ናቸው፤ እያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን የራሱን ሽልማት ይቀበላል። እኛ ከእግዚአብሔር ጋር አብረን የምንሠራ ነንና።” (1ቆሮ 3:6-9)


ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል በግልጽ እንደሚያስተምረን የሚያሳድግ እግዚአብሔር ነው። ይሁን እንጂ ሰዎች በዚህ የእድገት ሂደት ውስጥ ከእርሱ ጋር በመተባበር እንዲሰሩ የአማላካችን ሃሳብ ነው። በእርግጥም ምንም ያህል ታላቅ ሰብአዊ ጥረት ቢደረግ ያለ እግዚአብሔር ምንም አይነት እድገት አይኖርም። የህይወት ምንጩ እርሱ ነውና። ጳውሎስ ተመሳሳይን ሃሳብ በሌላ እነጋገር እንዲህ በማለት ይገልጻል።


“በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ የራሳችሁን መዳን ፈጽሙ፤ እንደ በጎ ፈቃዱ መፈለግንና ማድረግን በእናንተ ውስጥ የሚሠራ እግዚአብሔር ነውና።” (ፊል 2:12፣ 13)። እዚህ ላይ ሁለት ነገሮችን ልብ እንበል። አንደኛው እኛ ፈጽሙ የተባልነው ሲሆን፣ ሌላው ደግሞ እግዚአብሔር በእኛ ውስጥ የሚሰራው ነው። ኤለን ሃይት በዚህ ጥቅስ ላይ ማብራሪያ ስትሰጥ እንዲህ ትላለች:-


“በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ የራሳችሁን መዳን ፈጽሙ” ይህ ምን ማለት ነው? ይህ ማለት በየእለቱ በራሳችሁ ሰብአዊ ጥረትና ጥበብ አለመደገፍ ማለት ነው። አፋችሁ እንዳመጣላችሁ ከመናገርና በደመነፍስ ከመመራት መጠንቀቅ ማለት ነው። የልባችሁ ትእቢት፣ የአለም ፍቅርና የሥጋ ምኞት ጌታ ኢየሱስ ለእናንት ሊሰጥ ከሚናፍቀው ግሩም ጸጋ እንዳያጎድሎአችሁ መፍራት (መጠንቀቅ) ማለት ነው። በዚህ ጥቅስ ላይ የቀረበው የሰው ድርሻ ያለእግዚአብሔር ሰው በራሱ የሚሰራው ሥራ አይደለም። ይልቁንም በአምላክ ሃይልና ጸጋ ላይ በመደገፍ የሚያከናውነው ነው። ብዙዎች ይህንን ነጥብ ባለማስተዋል፣ ሰው ራሱን ለመለወጥ ያለምንም መለኮታዊ ሃይል በራሱ መስራት አለበት ይላሉ። ይህ ግን ከጥቅሱ ጋር አይስማማም። ሌሎች ደግም እግዚአብሔር መፈለግንም ማድረግንም ሁሉን አድርጎታልና ሰው ምንም ማድረግ የለበትም ይላሉ። ጥቅሱ የሚናገረው ለሰው ነፍስ ድነት የእኛ የመምረጥ ሃይልና ፈቃድ ለመለኮት ፈቃድ መገዛት እንዳለበት ነው። ይህ ደግሞ ከባድ ውጊያ ሲሆን ፈቃዳችንንና መንገዳችንን ለእግዚአብሔር ፈቃድና መንገድ እዲገዛ ቁርጥ ውሳኔ የምናደርግበት ነው።” (Our High Calling, 91)


እንግዲህ ማደግ የእግዚአብሔር ፈቃድ እንደሆነ፣ የሚያሳድገንም እርሱ ራሱ እንደሆነ በደንብ በማስተዋል፣ በእድገቱ ሂደት ደግሞ እኛም በፈቃደኝነት ከእርሱ ጋር መተባበርና ለእድገታችንም ከፍተኛ ትኩረት ልንሰጥ እንደሚገባን ቃሉ ያስተምረናል። ማደግ በምኞት ብቻ አይመጣም፤ ደግሞም ማደግ በእኛ ጥረት ብቻም አይከናወንም። ነገር ግን እግዚአብሔርና ሰብአዊ ፍጥረት የየራሳቸውን ሚና የሚጫወቱበት ጎዳና ነው።


ማደግ በተሰኘውን የአማርኛ ቃል እንደ ምጻረ-ቃል በመጠቅም ልናድግባቸው የሚገባንን ሦስት ዋነኛ አቅጣጫዎችን ልናስብ እንችላለን። አንደኛው፣ በማምለክ ማደግ ሲሆን ይህም ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ግንኙነት በዋናነት የሚመለክት ነው። ሁለተኛው የእድገት አቅጣጫ ደግሞ ደጋፊ በመሆን ማደግ ሲሆን ይህም በእግዚአብሔር ቤተሰብ ውስጥ ካሉት ወንድምና እህቶቻችን ጋር ያለንን ህብረት የሚመለክት ነው። ሦስተኛው፣ ግዴታችንን በመወጣት ማደግ ሲሆን፣ ይህም እንደ እግዚአብሔር መንግስት ወራሾች በዚህ መንግስት ውስጥ ያልተካተቱትን በማደም መንግስቱን የማስፋት ግዴታችንን መፈጸምን የሚመለክት ነው።


“በእነዚህ በሦስቱ አቅጣጫዎች እንዴት እያደግሁ ነው?” ብለን ራሳችንን ልንጠይቅ ይገባል። ለዚህ ጥያቄ ጥሩ ምላሽ ለመስጠት በእነዚህ በሦስት አቅጣጫዎች ማደግ ምን ማለት እንደሆነና እንዴትስ ማደግ እንደሚቻል በእግዚአብሔር መንፈስ መሪነት መመርመሩ ጠቃሚ ነው። በቀጣይ እትሞች እነዚህን ሦስት የእድገት አቅጣጫዎች በትናጠል ጠለቅ እድርገን እናጠናቸዋለን።


እስከዚያው፣ “በጌታችንና በአዳኛችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ዕውቀት እደጉ፤” 2 ጴጥ 3:18


በፓስተር መላክ አለማየሁ

14 views0 comments

Recent Posts

See All

እንደምን አደጋችሁ?

በፓስተር መላክ አለማየሁ ካለፈው የቀጠለ ባለፉት ሁለት ክፍሎች በመንፈሳዊ ሕይወታችን ስለ ማደግ ጠቅለል ባለ መልኩ መግቢያ የሚሆንን ሃሳብ ለማየት ሞክረናል። የፈጠረንና የዋጀን እግዚአብሔር ለእኛ ያለው አላማ እለት እለት ወደ በረከቱ ሙላት እንድናድግ መሆኑ ቃሉ አስተምሮናል። እንዲሁም፣ በጸጋ ማደግ የሚከቱትን ሦስት

“መንገድህን ለእግዚአብሔር አደራ ስጥ…”

በአለፉት ሶስት ወራት ጌታ በኢትዮጵያ አድቬንቲስት ቤተክርስትያን ከመስከረም 2010 ጀምሮ እስከ ህዳር መጨረሻ ድረስ ያደረገዉን ድንቅ ስራ ሳበሰር ታላቅ ደስታ ይሰማኛል፡፡ በኢትዮጵያ ዉስጥ ወንጌል የአልገባባቸዉ እጅግ ብዙ ስፈራዎች አሉ፡፡ ከእነዚህም መሀል አንዱ የዳሰነች ጎሳ ሲሆን፣ ጌታ ፈቅዶ በመጋቢት ወር አዲስ

"ለዘንድሮ ብቻ ተዋት"

በአገራችን 2010 አመተ ምህረት ከገባ 3 ወር አለፈው። በምዕራብ አገሮች ደግሞ በቅርቡ 2018 ይገባል። ሁሉም በየበኩሉ አዲሱን አመት ለመቀበል ሽርጉድ ይላል። በአገራችን "እንኳን ከዘመን ወደ ዘመን አሸጋገራችሁ" እንባባላለን። በምእራብ አገሮች ደግሞ "happy new year" ይባባላሉ። ትኩር ብለን ካሰብንበት ያ

የኢትዮጵያ አድቬንቲስት ቤተ ክርስቲያን ዋሺንግተን ዲሲ

© 2018 Ethiopian Seventh-day Adventist Church Washington DC

1700 Powder Mill Rd, Hillandale, MD 20903, U.S.A  301-356-5259

  • Facebook Social Icon
  • YouTube Social  Icon
  • Google Places Social Icon
  • Twitter Social Icon